let's talk
የባለአክሲዮኖች የመመስረቻ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

ለአስፓየር ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ማኅበር (በምሥረታ ላይ) ባለአክሲዮኖች በሙሉ

አስፓየር ማይክሮፋይናንስ አክሲዮን ማኅበር የባለ አክሲዮኖች መስራች ጠቅላላ ጉባኤ ጥቅምት 15/2018 ዓ/ም ከቀኑ 7 ፡30 ጀምሮ ካዛንችስ አካባቢ በሚገኘው ሂልተን ሆቴል የሚካሄድ በመሆኑ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ በስብሰባው ላይ እንዲገኙ በማለት የአደራጅ ኮሚቴው በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል።
የመደበኛና አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
 1.⁠ ⁠አክሲዮን ማኅበሩን ለማቋቋም የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን መሟላታቸውን ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ፣
 2.⁠ ⁠በአደራጅ ኮሚቴ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ፣
 3.⁠ ⁠የአክሲዮን ማኅበሩ የምስረታ ሂደት ኦዲት ሪፖርት ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
 4.⁠ ⁠የአክሲዮን ማኅበሩን ረቂቅ መመስረቻ ጽሑፍ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
 5.⁠ ⁠አደራጆች ለማህበሩ ምስረታ ያወጧቸውን ወጪዎች እና በገቡት ግዴታ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
 6.⁠ ⁠የአደራጅ ኮሚቴ ልዩ ጥቅም ልክ ተወያይቶ መወሰን፣
 7.⁠ ⁠የአክሲዮን ማኅበሩን የሚመሩ የዳይሬክትሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ማካሄድ፣
 8.⁠ ⁠የማኅበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ስለሚያስይዙት ዋስትና ተወያይቶ መወሰን፣
 9.⁠ ⁠የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የሥራ ዋጋ ተወያይቶ መወሰን፣
10.⁠ ⁠የማኅበሩን የወጪ ኦዲተር ሹመት ማካሄድና የሥራ ዋጋ ክፍያውን ተወያይቶ መወሰን፣
11.⁠ ⁠ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ በመቅረብ ቃለ ጉባኤውን እንዲፈርሙ ውክልና መስጠት
ማሳሰቢያ
▪ በጉባኤው ላይ በአካል መገኝት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮች አግባብ ባለው የመንግስት አካል የተረጋግጠ የውክልና ስልጣን ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ይዛችሁ በመቅረብ ወይም ሲኤምሲ አፍሪካ ኮንቬንሽን ሴንተር 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 209 በሚገኘው የድርጅቱ ጊዜዊ ማስተባበሪ ቢሮ ከጉባኤው ቀን ቀድሞ በመገኘት እና የውክልና ፎርም በመሙላት የጉባኤው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።
▪ በዕለቱ ጉባኤው ተወያይቶ የሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች በጉባኤው ባልተገኙ አባላት ላይ ጭምር የጸና ይሆናል፡፡
ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮቻችን +2519 929 91 84 64/ +2519 911 60 54 54/ +2519 1199 70 50 ማግኘት ይቻላል፡፡
የአስፓየር ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ማኅበር
አደራጅ ኮሚቴ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *